እንማማር
ድንጋይ ሳይፈለጥ ስሚንቶ ሳይቦካ፤
ዕዉቀት መሰብሰቢያ ቤት ይሰራል ለካ፤
ግድግዳሽ ሀበሻ ጉልላትሽ ራስ፤
ጎራው ላይ ተሰርተሽ ሳይነካሽ ነፋስ፤
ሰዉ ተሰብስቦ ከየዓለም ዳርቻ ፤
ቐጠሮዉን ፈቶ የ ዕዉቀቱን ስልቻ፤
እነካቺሁ እያለ የሚያካፍልብሽ፤
መከባበር ፍቅር ሰላም የሞላብሽ፤
አርዕስት ተነስቶ የሚወያይብሽ፤
ሀሳብ ከሃሳብ ጋር ተጋጭቶ ተፋጭቶ፤
መቐጫ አግኝቶለት በሃሳብ ተስማምቶ፡
ዉስጡ ተገናኝቶ ዘመድ ያፈራብሽ፤
በዉነት ይገባሻል እንማማር ቢሉሽ፤
በዉነት ይገባሻል እንማማር ቢሉሽ።
