የአዛውንቱ ብሶት
ረሃብ የለውጥ ዋዜማ ምልክትነቱን ዳግም እውን _ _ _ ?
አንድ ሕዝብ ታስተዳድረኛለህ ብሎ የመረጠውን መንግስት ማንነትና ምንነት በብእሩም ሆነ በአንደበቱ ለመግለጽ ይፋ መብት ሊኖረው እንደሚገባ ግልጽ ነው። ይህን ሃቅ የሰለጠኑት ሃገሮችም ሆኑ የ3ኛ ዓለም ሃገሮች መንግስታት አሌ አይሉት ም። ጥያቄው ያለው በ3ኛው ዓለም በተለይም በአፍሪካ የሚገኙ ሃገሮች ሕዝብ የሚያስተዳድረውን መንግስት የመምረጥ እድል አለው ወይ ? የሚለው ነጥብ ላይ ይመስለኛል። መልሱ ደግሞ የለም ነው። በአፍሪካ ሃገሮች መንግስታት የሚያስተዳድሩትን ህዝብ ይመርጣሉ እንጂ ህዝብ የሚያስተዳድረውን መንግስት ሲመርጥ አልታየም። IMF ን ላለማስቀየም ለይስሙላ የሚደረጉትን የምርጫ ድራማዎች እንዳሉ አልቆጥራቸውም። የሚያስተዳድረውን መንግስት የመምረጥ መብት የተነፈገ ህዝብ ደግሞ ያልመረጠውን መንግስት ማንነትና ምንነት በይፋ የመግለጽ መብት ይኖረዋል ብሎ መጠበቅ የአህያና የጅብን ፍቅር አይነት ተረት፤ ተረት ነው። አንድ ሃቅ ግን አለ። ” የአንድ መንግስት ማንነት በሚያስተዳድረው ሕዝብ የማሕበራዊ ሕይወት እድገትና ውድቀት ይለካል” የሚል። ትክክል።
Read the rest of this entry »